Content-Language: am ደጃዝማች ዑመር ሰመተር
header image




ደጃዝማች ዑመር ሰመተር



የኦጋዴኑ ጀግና የደጃዝማች
ዑመር ሰመተር የአርበኝነት ታሪክ













ትውልድና ዕድገት

Dejazmach Umer Semeter
የኦጋዴኑ አርበኛ ደጃዝማች ዑመር ሰመተር

Photo link
ዑመር ሰመተር በሶማሊያና በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ ካልካይ በተባለው ስፍራ በ1880 ዓ.ም. ተወለዱ፡፡
በ1888 ዓ.ም. ፋሽስት ኢጣሊያ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያን ሲወር ገና የ 8 ዓመት ልጅ ነበሩ፡፡
የልጅ ልጅ ልጃቸው የሆነው ጉሌድ አህመድ ሰላድ እንደሚያስረደው፤ ዑመር ሰመተር አሉላን በተባለው ቦታ ተወልደው እዚያው እንዳደጉ ይናገራል፡፡
የቁራን ትምህርት ከተከታተሉም በኋላ ለተጨማሪ ትምህርት ወደ ኤደን ሀገር ሄደው ትምህርታቸውን ከተከታተሉ በኋላ ወደ ሀገር ቤት ተመልሰዋል፡፡

የዑመር ሰመተር የአርበኝነት ተግባር

ወደ አገራቸውም ተመልሰው የቁራን ትምህርት በማስተማር ላይ ሳሉ ፋሽስት ኢጣሊያ ለሁለተኛ ጊዜ ኢትዮጵያን ስትወር የ48 ዓመት ጎልማሳ ስለነበሩ ሀቢዮን ወደተባለው የኢጣሊያ ወታደሮች ወደሰፈሩበት ቦታ በማምራት እነርሱን መዋጋት ጀመሩ፡፡
ከዚያም ወደ ደጋሐቡር በመሄድ ከጦር አለቆቻቸው መሪዎች ከነበሩት ከደጃዝማች ገብረ ማሪያም ጋሪ ጋር ተገናኙ፡፡
ደጃዝማች ገብረ ማሪያምም የዑመር ሰመተርን ጀግንነት ተመልክተው ነበርና ከኦጋዴን አካባቢ ከነበሩት ወታደሮች መልምለው እንዲቀጥሩ ለዑመር ሰመተር ፈቀዱላቸው፡፡
በዚህም ጊዜ ዑመር ሰመተር የፊታውራሪነት ማዕረግ እንዲሰጣቸው ተደረገ፡፡
ፊታውራሪ ዑመር ሰመተር ከደጃዘማች ነሲቡ ዘአማኑዔልና ከደጃዝማች አፈወርቅ ወልደ ሰማያት ጋር ሆነው በጋራ ተዋግተዋል፡፡
በተለይ ለሀገራቸው ነፃነት ሲሉ ደጃዝማች አፈወርቅ ወልደ ሰማያት በጦር ሜዳ መስዋዕት ሲሆኑ አረበኞችን እያረጋጉ ጦሩን ይመሩ እንደነበረ ተዘግቧል፡፡
ፊታውራሪ ዑመር ሰመተር ሰላዮቻቸውን ወደ ሶማሊያ በመላክ የጠላትን እንቅሰቃሴ በመሰለል የሀገራቸው አርበኞች ቅድሚያ ጥንቃቄ እንዲወስዱ እገዛ አድርገዋል፡፡
በወልወል ግጭት ወቅትም የምስራቅ አፍሪቃ የኢጣሊያ ጦር መሪ ከነበረው ደልደሎ ከተባለው ሰው ጋርም ፊታውራሪ ዑመር ሰመተር ጦርነት ገጥመው መሪውን ገድለው ትጥቁን እንደማረኩ ተተርኳል፡፡
በተለይ 6 ባታሊዮን ጦር ይዞ ወልወል ላይ ጦርነት በከፈተው የኢጣሊያ ጦርነት ላይ ተገኝተው ከፍተኛ የአርበኝነት ተጋድሎ ማድረጋቸው ይነገራል፡፡
Dejazmach Umer Semeter
የኦጋዴኑ አርበኛ ደጃዝማች ዑመር ሰመተር

Photo link
ኤልቦር በተባለው ስፍራ በዑመር ሰመተር ላይ ያንዣበበው አደጋ አስደንጋጭ ነበር፡፡
በ 6 ባታሊዩን ጦር የተከበበው የፊታውራሪ ዑመር ሰመተር ጦር በጀግንነት ምሽጉን ሰብሮ በመውጣት፤ የመከላከያ ወረዳ በመያዝ ጦራቸውን መልሰው ከአደራጁ በኋላ በጠላት ላይ የመልሶ ማጥቃት እርምጃ ለመሰንዘር ዝግጅታቸውን ጨረሱ፡፡
በኋላም በ1930 ዓ.ም. በአንድ ቀን ሌሊት በ 6 የኢጣሊያ ጦር ላይ ድንገተኛ ጥቃት በማድረስ ብዙ የጠላትን ወታደሮች በመግደልና በርካታ የጠላትን መሣሪያዎች በመመራክ ከፍተኛ ጀብዱ ፈጽመዋል፡፡
ዑመር ሰመተር በተካፈሉባቸውም የውጊያ አውዶች ሁሉ ወንድሞቻቸውና 54 የሚደርሱ ልጆቻቸው ይሳተፉ ስለነበር ከ 11 በላይ ልጆቻቸው በጦርነት ግንባር ሲሰው በሌሎች ወነድሞቻቸውም ላይ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
በተለይ ሳላድ የተባለው ልጃቸው አይኑ ጠፍቶ እግሩም ተቆርጦ ነበር፡፡
ሌሎች የቤተሰባቸው አባላትም ለከፍተኛ ጉዳት መዳረጋቸው ይተወሳል፡፡
ፋሽስት ኢጣሊያ የእርቅ ድርድር ለማድረግ በሞከረበት ወቅትም ዑመር ሰመተር እጃቸው ተይዞ ይሰጠኝ በማለት ጥያቄ ሲያቀርቡ ዑመር ሰመተር ጥያቄውን ውድቅ አድርገውታል፡፡
ከጥቂት ጊዜ በኋላም ፋሽስት ኢጣሊያ ወረራውን በኢትዮጵያ ሰሜን ግንባርና በደቡብ ግንባር ሲያስፋፋ ዑመር ሰመተር መረጃው ስለነበራቸው ጦራቸውን አዘጋጅተው ይጠባበቁ ነበር፡፡

በደቡብ ግንባር የፈፀሙት ተጋድሎ


Umer Semeter High School Addis Ababa
ኮልፌ አጣና ተራ የሚገኘው የዑመር
ሰመተር አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት

ምስጋና፤ ለደቻሳ አንጌቻ Photo link
በኦጋዴን ድንበር የወልወል ግጭት ወቅትም ወደ ወልወል እና ወደ ቆራሄ በማምራትም ከጠላት ጋር መፋለማቸውን ተያያዙት፡፡
የጠላት ጦርም በደቡብ ግንባር ገርገስውቤ ወደተባለው ስፍራ እንደተጠጋ መረጃው የነበራቸው ዑመር ሰመተር፤ ተወርዋሪ ጦራቸውን ወደ ስፍራው ይዘው ሄደው ድንገተኛ ውጊያ በመክፈት በጠላት ላይ ከፍተኛ ድል አስመዝግበዋል፡፡
ዑመር ሰመተር በርካታ ውጊያዎችን በፈፀሙበት ወቅት በ 6 እና በ 7 ጥይቶች ተመተው በከባድ ሁኔታ ቆስለው ስለነበረ ውጊያውን መቀጠል የማይችሉበት ደረጃ ላይ ስለደረሱ ወደ ጅግጅጋ ወሰዷቸው፡፡
እርሳቸው ግን ብዙም ሳይቆዩ የአካባቢውን ሰዎች በማስተባበር ሸቀጦቻቸውን እየሸጩ ጥይት እና መሣሪያ እየገዙ ለሚዋጋው የኢትዮጵያ ወታደር እንዲላክ ያስተባብሩ ነበር፡፡
ሆኖም የአርበኛው ቀኛዝማች ዑመር ሰመተር ቁስላቸው እየበረታ በመሄዱ ህክምና እንዲያገኙ በማሰብ ወደ ሀርጌሳ ተልከው በኬንያ በኩል ወደ ለንደን ተወስደው ጦርነቱ እስከሚያበቃ ድረስ እዚያው እንዲቆዩ ተደረገ፡፡
በመጨረሻም የሀገራቸው ነፃነት ሲመለስ ከንጉሠ ነገሥቱ ጋር አብረው ተመለሱ፡፡
ከጊዜ በኋላ በዑመር ሰመተር ሰውነት ውስጥ የቀሩትን ጥይቶች ለማሶጣት ወደ ውጭ ሀገር ተልከው አምስቱን ጥይቶች ብቻ አሶጥተው ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የልጅ ልጃቸው ወይዘሮ አይሻ ሰላድ ዑመር ሰመተር ያስረዳሉ፡፡
ከነፃነት በኋላም ለሀገራቸው ነፃነት ሲሉ ከጠላት ጋር አብረዋቸው የተዋጉትን አርበኞችና የአርበኞች መሪዎችን በማሰባሰብ የደጃዝማችነት ማዕረግ በንጉሠ ነገሥቱ በማሰጠት በኦጋዴን ግዛት የጅጅጋ አውራጃዎች ገዥ ሆነው እንዲሾሙ አድርገዋል፡፡
ደጃዝማች ዑመር ሰመተር በሰውነታቸው ውስጥ የቀሩት ጥይቶች ሰላሎጡላቸው ቁስላቸው እያመረቀዘ ሰለተቸገሩ ወደ ሐረር ከተማ በመሄድ ሐኪሞች ባሉበት ቦታ ሁሉ እየተዘዋወሩ ለመታከም ጥረት ቢያደርጉም ለመዳን ግን ሳይችሉ ቀሩ፡፡

ህልፈተ ሕይዎት

ደጃዝማች ዑመር ሰመተር በጎልማሳነት ዕድሜያቸው በተወለዱ በ56 ዓመታቸው መጋቢት 10 ቀን 1936 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
አሰከሬናቸውም ሐረር በሚገኘው የአብደል መካነ መቃብር፤ የሐረሩ መስፍን ልዑል መኮንን ኃይለ ሥላሴ፤ መሳፍንቶቻቸውን አስከትለው በተገኙበት እና እንዲሁም ሙስሊሙም ሆነ ክርስቲያኑ ሕብረተሰብ ሳየቀር ሁሉም ወጥቶ በወታደራዊ ስነ ሥረዓት ታጅቦ የቀብራቸው ሥነ ሥረዓት ተፈጽሟል፡፡

ደጃዝማች ዑመር ሰመተር ለሀገራቸው ነፃነት ላበረከቱት ከፍተኛ ተጋድሎና ለአርበኝነታቸው መታሰቢያ ይሆን ዘንድ፤ ምንም እንኳን በቂ ባይሆንም አንዋር መስኪድ አጠገብ ትምሕርት ቤት ታንጾላቸዋል፡፡
እንዲሁም ኮልፌ አጣና ተራ የሚገኘው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በስማቸው እንዲጠራ ተወስኖል፡፡

ጀግናው አርበኛ ዑመር ሰመተር ከመሞታቸው በፊት የተናገሯቸው ወርቃማ ቃላት

ጀግናው አርበኛ ደጃዝማች ዑመር ሰመተር ሕይዎታቸው ከማለፉ በፊት የሚከተሉትን ጊዜ የማይሽራቸው ወርቃማ ቃላትን ተናግረዋል፡፡






ምንጭ፤
  1. Addis 1879 /አዲስ 1879 …ምስጋና፤   ለአዲስ 1879 ፕሮግራም አዘጋጆች
  2. የትረካው አጃቢ ሙዚቃ፣ ዋሽንት - በአንሙት ክንዴ   ዩቲውብ