የሚያውቁትን ለማስታወስ እንዲረዳዎት ሳጥኑ ውስጥ ያሉትን ቀላል ጥያቄዎች አንብበው ለመመለስ ይሞክሩ የጥያቄውን መልስ ሳጥኑን በመጫን ያገኙታል
የተጫኑትን የጥያቄ ሳጥን ወደ ቀድሞው ቦታ ለመመለስ በድጋሚ ሳጥኑን ይጫኑት
በ ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት
↑( ስለ ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ የበለጠ ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ)
1. በዐድዋ ጦርነት የገጠመውን ሀፍረት ለመሻር እና፣
2. እጅግ ለምና በከርሰ ምድር ሐብቷ የበለፀገችውን ኢትየጵያን ለመቆጣጠር ነበር፡፡
ደጃዝማች ኃይለ ሥላሴ ጉግሳ ይባላል፡፡
ኃይለ ሥላሴ ጉግሳ፤ ከአፄ ዮሐንስ የልጅ ልጅ የሚወለድ ሲሆን ባለቤቱም የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሁለተኛ ልጅ
ልዕልት ዘነበወርቅ ነበሩ፡፡
ከሃዲው ኃይለሥላሴ ጉግሣ
ኃይለ ሥላሴ ጉግሳ በተሰጠው ማዕረግ ደስተኛ ስላልነበረ ቂም መቋጠሩን የተረዱት የኢጣሊያ አዛዦችም ከራስ ስዩም
መንገሻ ነጥቀን ሙሉ ትግራይን እንሰጥሀለን ብለውት ስለነበረ ይህን ተሰፋ አድርጎ ከጠላት ጋር ወግኖ አገሩን ሲወጋ
ቆይቶ በኋላም ጣሊያኖች የተመኘውን የራስነት ማዕረግ ብቻ ሰተውት ነበር፡፡
ጣሊያኖች ኢትዮጵያን ለቀው ከወጡ በኋላ ግን በአገር ክህደት ወንጀል ተከሶና የተሠጠውም የራስነት ማዕረግ ተገፎ
ለብዙ ዘመናት በእስር ቤት ከቆየ በኋላ ሕይወቱ አልፏል፡፡
ዶክተር መላኩ በያን ይባላል፡፡
ዶክተር መላኩ በያን
ዶክተር መላኩ በያን የተወለደው በወሎ ጠቅላይ ግዛት ሲሆን በ30 ዓመት እድሜው ወደ አሜሪካ ለትምህርት
ተልኮ ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ዝነኛና ታዋቂ ከሆነው አፍሪካ አሜሪካዉያን ከሚማሩበት ከሃዋርድ ዩኒቨርሲቲ
በሕክምና ዶክትሬት ዲግሪ የተመረቀ ብቸኛውና የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የሕክምና ዶክተር ነበር፡፡
ዶክተር መላኩ፤ በአሜሪካ ምድር “የኢትዮጵያ የዓለም ፌደሬሽን” የተሰኘውን ድርጅት በኒውዮርክ ከተማ ነሐሴ
19 ቀን 1929 ዓ. ም. በመመስረት ታላቅ ተግባር የፈፀመ እውቅ ኢትዮጵያዊ ምሁር ነበር፡፡
( ስለ ንዶክተር መላኩ በያን የበለጠ ለማንበብ) → ይህን ሊንክ ተጭነው ክፍል 19ን ያንብቡ
ኢምፔሪያል ኢትዮጵያ አቪየሽን (Ethiopian Imperial Aviation)
ኮሎኔል ስምረት መድኃኔ ይባላሉ፡
ኮሎኔል ስምረት መድኃኔ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ታህሳስ 12 ቀን 1938 ዓ. ም. ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ ሙሉ በሙሉ በአሜሪካኖች
ይመራ ነበር፡፡ ከ26 ዓመታት ቆይታ በኋላ ኮሎኔል ስምረት መድኃኔ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ዋና ሥራ
አስኪያጅ ሆነው ተሾሙ፡፡
የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አባት
ልዑል ራስ መኮንን ወልደ ሚካኤል ይባላሉ::
(ስለ ልዑል ራስ መኮንን ወልደ ሚካኤል የበለጠ ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ) ↑
ልዑል ራስ መኮንን ወልደ ሚካኤል
ቀዳማዊ ምኒልከ
በአክሱም ፅዮን የሚገኘው
የቀዳማዊ ምኒልክ ስዕል
በአክሱሙ ንቡረዕድ ይስሐቅ በ14ኛው ክፍለ ዘመን በግዝ ቋንቋ በተጻፈው ክብረ ነገሥት ላይ እንደተመዘገበው
የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ንጉሥ ምኒልክ ከንጉሥ ሰለሞንና ከንግሥተ ሳባ የተወለደ ነው፡፡
ንጉሥ ሰለሞን የቃል ኪዳኑን ታቦት ለልጁ ለምኒልክ በስጦታ ከሰጠው በኋላ ምኒልክ በርካታ እስራኤላውያንን
አስከትሎ ወደ ሀገሩ ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሰ በኋላ እናቱ ንግሥት ሳባ ስትሞት በአንድ ሺህ ዓመተ ዓለም
ዘውዱን ድፍቶ ቀዳማዊ ምኒልክ ተብሎ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያው ንጉሥ መሆን ቻለ፡፡
ቀዳማዊ ምኒልክ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ከሆነ በኋላ “የመጀመሪያውን ሰለሞናዊ ሥርዎ መንግሥት”
(Solomonic Dynasty) መሠረተ፡፡
ከቀዳማዊ ምኒልክ ጀምሮ ለ 3ሺህ ዘመናት የቆየው ሰለሞናዊው ሥርዎ መንግሥት፤ ደርግ በ1966 ዓ. ም. በመፈንቅለ መንግሥት ሥልጣን ሲረከብ፤ 225ኛው የ ሰለሞናዊው ስርዎ መንግሥት የመጨረሻ ፍጻሜው ሆነ፡፡
(ስለ ዳግማዊ አፄ ምኒልክ የበለጠ ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ) → ዳግማዊ አፄ ምኒልክ
(ስለ ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የበለጠ ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ) → ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ
ዶክተር ስንዱ ገብሩ ይባላሉ፡፡
ዶክተር ስንዱ ገብሩ
ዶክተር ስንዱ፤ በውጥጭ አገር ትምህርት የቀሰሙ ሲሆን የታሪክ፣ የእንግሊዝኛና የፈረንሳይኛ ቋንቋዎችን ተምረዋል፡፡
የስንዱ ገብሩ ወላጅ አባት ከንቲባ ገብሩ፤ ታዋቂ ዲፕሎማት፣ የመጀመሪያው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል
ፕሬዝደንት፤ ኢጣሊያ ከኢትዮጵያ ለቃ ከወጣችም በኋላ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፕሬዝደንት፤ በዳግማዊ ምኒልክ
ጊዜም የመጀመሪያው የጎንደር አስተዳዳሪ ሆነው ያገለገሉ ናቸው፡፡
የከንቲባ ገብሩ ታናሽ እህት የውብዳር ገብሩ ይባላሉ፡፡ ከመነኮሱም በኋላ እማሆይ ጽጌ ማሪያም ተባሉ፡፡
ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ ይባላሉ፡፡
ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ
ሐምሌ 20 ቀን 1869 ዓ. ም. ምንጃር የተወለዱት ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ፤ ከዓድዋ ድል በኋላ በሁለተኛው ዓመት ጀርመን አገር ተልከው የመጀመሪያ የሆነውን መዲናና ዘለሰኛ የያዘ የአማርኛ ዜማ በሸክላ ከአስቀረፁ በኋላ ሸክላውን ያስቀረፀው ኩባንያ የድካምዎ ዋጋ ይሁንዎ ብሎ የሰጣቸውን 16 ሺህ
የጀርመን ፍራንክ ተቀብለው ወደ አገራቸው ተመልሰዋል፡፡
ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ የብዙ ሙያዎች ባለቤት በመሆናቸው፤ ገጣሚ፣ ጥበበኛ፣ ሰዓሊ፣ ቀራፂ፣ የፖለቲካ ሹም፣
አሳሽና የተዋጣለት ፎቶግራፍ አንሺ እንደነበሩ ተዘግቧል፡፡ ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ በ88 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም
በሞት ተለይተዋል፡፡
የነጋድራስ ተሰማ እሸቴ ልጅ የነበሩት አቶ ይድነቃቸው ተሠማ፤ በቅዱስ ጊዮርጊስ የእግር ኳስ ክለብ ለ27 ዓመታት የተጫወቱ፣
የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽንን ከአቋቋሙት ውስጥ አንዱ የሆኑ፣ የእግር ኳስን ሕግ ወደ አማርኛ የተረጎሙ፤ የዓለም
አቀፍ ኦሎምፒክ ኮሚቴና የፊፋ አባል የነበሩና በመጨረሻም የአፍሪካ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት የነበሩ ናቸው፡፡
የኢትዮጵያና ብሎም የአፍሪካ የዘመናዊ ስፖርት አባት የተባሉት አቶ ይድነቃቸው ተሠማ ነሐሴ 14 ቀን 1979 ዓ. ም. በተወለዱ በ66
ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ በ 1900 ዓ. ም. ካሳተሙት የሙዚቃ ሸክላ የተወሰደውን የ 1 ደቂቃ ሙዚቃ ቀጥለው ያዳምጡ፡፡
( ምስጋና ለ፤ Ibex Media)
እማሆይ ፅጌ ማሪያም ገብሩ ይባላሉ፡፡
እማሆይ ፅጌ ማሪያም ገብሩ
እማሆይ ፅጌ ማሪያም ከመመንኮሳቸው በፊት የውብዳር ገብሩ ይባሉ ነበር፡፡ የዶክተር ስንዱ ገብሩ እህት ናቸው፡፡
ገና በ19 ዓመት ለጋ እድሜያቸው ከቤተሰቦቻቸው ጠፍተው ወደ ግሸን ማርያም በመሄድ ምንኩስና ተቀብለዋል፡፡
እየሩሳሌምም ለ30 ዓመታት ያህል ኖረዋል፡፡ እማሆይ ፅጌ ማርያም 99ኛ ዓመታቸውን አክብረው 100ኛ ዓመታቸውን
እንደያዙ ይነገራል፡፡
ዳግማዊ አፄ ምኒልክ
↑ ( ስለ ዳግማዊ አፄ ምኒል የበለጠ ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ)
እቴጌ ጣይቱ ሆቴል
እቴጌ ጣይቱ ሆቴል፤ ከዓድዋ ድል ከ10 ዓመት በኋላ በ1998 ዓ. ም. አሁን ፒያሣ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ
ከተሠራ በኋላ እቴጌ ጣይቱ ራሳቸው እያሰተናገዱና በነፃም እየጋበዙ ተጋባዥ እንግዶችን የሆቴል አገልግሎት እንዳለማመዱ ተዘግቧል፡፡
(ስለ እቴጌ ጣይቱ የበለጠ ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ)→ እቴጌ ጣይቱ
ጀነራል አለልቤርቶኒ ይባላል፡፡
በዓድዋ ጦርነት ወቅት ፋሽስት ኢጣሊያ ያሰለፈቻቸው ጀነራሎች ከዋናው አዛዥ ጋር አምስት ሲሆኑ ስማቸውም፤
በኢትዮጵያውያን የተማረከው
ጀነራል አልቤርቶኒ
1. ጀነራል ባራቲዬሪ - ዋና የጦር አዛዥ፣
2. ጀነራል አሪሞንዲን፣
3. ጀነራል ዳቦር ሜዳ፣
4. ጀነራል አለልቤርቶኒ እና
5. በወቅቱ አዲስ ሹመት አግኝቶ የነበረው ጀነራል ኤሌና ይባላሉ፡፡