Content-Language: am ደጃዝማች አያሌው ብሩ
header image



ደጃዝማች አያሌው ብሩ



የደጃዝማች አያሌው ብሩን የሕይዎት ታሪክ ያዳምጡ












1. ትውልድና የሕይዎት ዘመን

Dejazmach Ayalew Birru
ደጃዝማች አያሌው ብሩ
አያሌው ብሩ፤ የማይጨው አርበኛ ከነበሩት ከአባታቸው ከራስ ብሩ ወልደ ገብርኤል እና ከናታቸው ከወይዘሮ ገሠሠ ማርሶ በ1984 ዓ.ም. በቤገምድር ጠቅላይ ግዛት ተወለዱ፡፡
አያሌው ብሩ የእቴጌ ጣይቱ ብጡል ዘመድ ሲሆኑ እቴጌ ጣይቱም የራስ ጉግሣ ወሌ አክስት ናቸው፡፡
አያሌው ብሩ ጥር 10 ቀን 1910 ዓ.ም. ወይዘሪት ሆይ ማንያህሉሽ ካሣን አገቡ፡፡
ማንያሂሉሽ የልዑል ራስ ካሣ ኃይሉ ዳርጌ ሁለተኛ ልጅ ናቸው።
አያሌው ብሩ እና ማንያህሉሽ ካሳ ልጆች ነበሯቸው።
በ 1920 ዓ.ም. መገባደጃ ላይ የራያ ኦሮሞ በወሎ ክፍለ ሀገር አመፅ ባስነሱበት ወቅት፤ ልዑል አልጋ ወራሽ ተፈሪ መኮንን አመፁን ለማብረድ ለብዙ አጎራባች የአውራጃ ገዥዎች ጥሪ አቅርበው ነበር፡፡
አያሌው ብሩ ፣ የሰሜን ሹም እንደመሆናቸው መጠን ከተጠሩት ገዥዎች አንዱ ነበሩ።
ከሌሎች ጥሪ ከተደረገላቸው የአውራጃ ገዥዎች ይልቅ፤ ደጃዝማች አያሌው ብሩ ፣ በላስታ የተነሳውን አመፅ ለማብረድ በብርቱ ሰርተዋል፡፡
የቤገምድሩ ገዥ የነበሩት ራስ ጉግሳ ወሌ፤ ቀኛዝማች አያሌው ብሩ አለመኖራቸውን በመገንዘብ አብዛኛውን የአያሌው ብሩን ግዛት በቁጥጥራቸው ሥር አደረጉት፡፡
ራስ ጉግሳ ወሌና አያሌው ብሩ ሁለቱም የህትማማች ልጆች ሲሆኑ ከ እቴጌ ጣይቱም ጋር በቅርብ ይዛመዳሉ፡፡
በ 1928 ዓ.ም. ራስ ጉግሳ ወሌ በንጉሥ ተፈሪ ላይ በማመፅ ንጉሡን ከሥልጣናቸው ለማውረድ በርካታ ሠራዊት አደራጁ፡፡
አያሌው ብሩ፤ አንችም በተባለው ስፍራ ከራስ ጉግሳ ጋር ባካሄዱት ጦርነት ጀግንነትን ፈጽመዋል፡፡
ምንም እንኳን አያሌው ብሩ በአንችም ጦርነት ጀግንነት ቢፈጽሙም፤ የእቴጌ ጣይቱ የቅርብ ዘመድ ናቸው በሚል ሰበብ የራስነት ማዕረግ ሳያገኙ ቀርተዋል፡፡
ይህን የአያሌው ብሩን ልፋት በከንቱ መቅረት የተመለከተው የአገራቸው ተወላጆች፤
“አያሌው ሞኙ፣ ሰው አማኙ፤ ሰው አማኙ፤”
የሚል ግጥም ገጠመላቸው፡፡
በኋላም በ 1923 ዓ.ም. አያሌው ብሩ የፊታውራሪነት ሹመት ከተሰጣቸው በኋላ የጦር ምኒስትር ሆኑ፡፡
ብዙም ሳይቆዩ ወደ አርሲ ጠቅላይ ግዛት በግዞት ተላኩ፡፡

2. የአርበኝነት ዘመን

Dejazmach Ayalew Birru
የደጃዝማች አያሌው ብሩ ጦር
በ 1928 ዓ.ም. ፋሽስት ኢጣሊያ ወረራ ሲፈጽም፤ ፊታውራሪ አያሌው ብሩ ከግዞት ተመልሰው ከንጉሠ ነገሥቱ ጋር ወደ ጦር ግንባር ለመዝመት ሲነሱ ከሙሉ ልባቸው አልነበረም፡፡
ይሁን እንጅ የኋላ ኋላ ፊታውራሪ አያሌው ብሩ፤ ታላቅ ዝና የነበራቸው ደፋር የጦር መሪ ነበሩ።
ፊታውራሪ አያሌው ብሩ ከራስ እምሩ ኃይለ ሥላሴ ጦር ጋር በመቀናጀት የገና ጥቃት ተብሎ በሚጠራው በጣሊያኖች ላይ በተወሰደው ጥቃት ላይ በዘማቻው ላይ ተሳትፈዋል፡፡
ከራስ እምሩ ኃይለ ሥላሴ ጦር ጋር በመቀናጀትም ደምበጊና በተባለው የጠላት ይዞታ ላይ በተደረገው ውጊያ የእርሳቸው ጦር ጉልህ ሚና ተጫውቷል፡፡

3. ከነፃነት በኋላ

ደጃዝማች አያሌው ብሩ በሕይወት ዘመናቸው በበርካታ ግዛቶች ላይ ተሹመው አገልግለዋል፡፡
ከ 1908 ዓ.ም. ጀምሮ የወገራ አውራጃ ሹም ነበሩ።
ከ 1920 ዓ.ም. ጀምሮ የስሜን ጠቅላይ ግዛት ሹም ነበሩ።
ከነፃነት በኋላ በ 1933 ዓ.ም. እንግሊዞች ባካሄዱት የምስራቅ አፍሪካ ዘመቻ ወቅት አያሌው ብሩ እንደገና ከንጉሠ ነገሥቱ ጎን በመሆን በበጌምድር ጠቅላይ ግዛት ለሚገኙት የአርበኞች አዛዥ ሆነው ተሹመዋል፡፡
በኋላም ደጃዝማች አያሌው የራስነት ማዕረግ ተሰቷቸው የካፋና የጅማ ሹም ሆኖ አገልግለወል።
ልጅ እያሱ ከስልጣን ከወረዱ በኋላም ከ 1909 ዓ.ም ጀምሮ ደጃዝማች አያሌው ብሩ ለአንድ ዓመት ያህል የንግሥተ ነገሥቱ የጦር ዋና አዛዥ ሆነው በልዑል ራስ ተፈሪ መኮንን ተሹመዋል፡፡



ምንጭ፤
  1. ከዊኪፒዲያ (በድረ ገጽ አዘጋጁ የተተረጎመ)
  2. የትረካው አጃቢ ሙዚቃ፣ ዋሽንት - በአንሙት ክንዴ   ዩቲውብ